ታላቁ ሐዋርያዊ አባት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሐምሌ 22 ቀን 1982 ዓ.ም ነበር። ስለ ታላቅ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸው፣ ዘመን ስለሚሻገር ሥራቸው ሁል ጊዜም እናስታውሳቸዋለን። ዕለቱን ለመዘከር የሚከተለውን ግጥም ያንብቡ።
+++++++
በሰንበት ዕለት ንጋት ብርሃን በዝዋይ ጠለቀች፣
የጨረቃ ከዋክብት ውበታቸው በቅጽበት አፍታ አለፈች።
አሀዱ ብሎ ካህኑ - እትዉ ሲለን ዲያቆኑ፣
ለካስ ስንብቱ ለጳጳስ ኖሯል - መርዶው ደረሰ ወዲያውኑ።
ጎርጎርዮስ ኢትዮጵያዊ ብርሃን ዘደቡብ ኢትዮጵያ ፣
አብነትህ ፈክቶ ወጣ - ምልክት ስንሻ ሐዋርያ።
የትም ወድቆ አልቀረም - የተዘራው የወንጌል አዝመራ፣
ያስተማርከው የወንጌል ቃል - እነሆ መቶ አፈራ።
ክህነት ባንተ ከበረች - ጵጵስና አማረች ባንተ ፣
ዘብ ቆመህ ብትጠብቃት - አምላክ ባንተ ተደሰተ።
እንዲህ እንጂ ኖላዊ - እንዲህ እንጂ አባትነት፣
ገና በ50 ዘመን - የሺህ ዓመት ሥራ መሥራት።
እንዲህ እንጂ ጵጵስና - እንዲህ እንጂ አርአያነት፣
ሥጋን ለነፍስ አስገዝቶ - በመሞት ሕይወትን ማግኘት።
በጽሑፍህ ብርሃን ጸዳል - ከድንቁርና ጨለማ ወጣን፣
በአባትነትህ ተመክተን - የዛሬውን ቀቢጸ ተስፋ አለፍን።
እኔስ ተክልዬን አላየሁም - አሊያ ሐዋርያውን አትናቴዎስ፣
ጳውሎስን አላየሁት ሲሰብክ - አልሰማሁት የዋሁን ጴጥሮስ።
አላየችም ዓይኔ በዓይኗ - የጊዮርጊስን ሰማዕትነት፣
የተሰዓቱን ቅዱሳን ገድል - የጻድቃኑን መውረድ መውጣት፣
አይታለች ዓይኔ ጎርጎሪን - ሲበላው የእግዜር ቤት ቅናት፣
ሰምታለች ዕዝነ ልቡናዬ - የታላቁን አባት ቃላት።
(ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ፤ 1982 ዓ.ም ዝዋይ እና 2001 ዓ.ም፣ አሜሪካ)
+++++++
በሰንበት ዕለት ንጋት ብርሃን በዝዋይ ጠለቀች፣
የጨረቃ ከዋክብት ውበታቸው በቅጽበት አፍታ አለፈች።
አሀዱ ብሎ ካህኑ - እትዉ ሲለን ዲያቆኑ፣
ለካስ ስንብቱ ለጳጳስ ኖሯል - መርዶው ደረሰ ወዲያውኑ።
ጎርጎርዮስ ኢትዮጵያዊ ብርሃን ዘደቡብ ኢትዮጵያ ፣
አብነትህ ፈክቶ ወጣ - ምልክት ስንሻ ሐዋርያ።
የትም ወድቆ አልቀረም - የተዘራው የወንጌል አዝመራ፣
ያስተማርከው የወንጌል ቃል - እነሆ መቶ አፈራ።
ክህነት ባንተ ከበረች - ጵጵስና አማረች ባንተ ፣
ዘብ ቆመህ ብትጠብቃት - አምላክ ባንተ ተደሰተ።
እንዲህ እንጂ ኖላዊ - እንዲህ እንጂ አባትነት፣
ገና በ50 ዘመን - የሺህ ዓመት ሥራ መሥራት።
እንዲህ እንጂ ጵጵስና - እንዲህ እንጂ አርአያነት፣
ሥጋን ለነፍስ አስገዝቶ - በመሞት ሕይወትን ማግኘት።
በጽሑፍህ ብርሃን ጸዳል - ከድንቁርና ጨለማ ወጣን፣
በአባትነትህ ተመክተን - የዛሬውን ቀቢጸ ተስፋ አለፍን።
እኔስ ተክልዬን አላየሁም - አሊያ ሐዋርያውን አትናቴዎስ፣
ጳውሎስን አላየሁት ሲሰብክ - አልሰማሁት የዋሁን ጴጥሮስ።
አላየችም ዓይኔ በዓይኗ - የጊዮርጊስን ሰማዕትነት፣
የተሰዓቱን ቅዱሳን ገድል - የጻድቃኑን መውረድ መውጣት፣
አይታለች ዓይኔ ጎርጎሪን - ሲበላው የእግዜር ቤት ቅናት፣
ሰምታለች ዕዝነ ልቡናዬ - የታላቁን አባት ቃላት።
(ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ፤ 1982 ዓ.ም ዝዋይ እና 2001 ዓ.ም፣ አሜሪካ)
No comments:
Post a Comment